Haile Fida Ena Yegle Tezeta

€9.99
In stock
SKU
Haile Fida Ena Yegle Tezeta

ይህንን መጽሐፍ ለማሰናዳት የገፋፉህን ምክንያቶች ተመልክቻለሁ። ተገቢም ሆነው አግንቻቸዋለሁ። ሌሎችም ምሁራን በዚህ ጉዳይ የዚያን ዘመን ትዝታዎቻቸውን ቢያካፍሉ ለአዲሱ ትውልድ እጅግ ጠቀሚ መሆኑን በማሳመር ይህንን መጽሓፍ በዚህ መልክ ማበርከትህ ታላቅ አስተዋጽኦ ሆኖ አግንቸዋለሁ።

ነገደ ጎበዜ (ዶ/ር)

አማረ ተግባሩ በኢትዮጵያ የተማሪዎች ማኅበራት ጀምሮ ከዚያም ከየካቲት 66 በኋላ ከተመሪዎች ንቅናቆቄ በፈለቈት የግራ ድርጅቶች መካከል በተለይ አብዮቱንና ደርግን በተመለከተ የተነሱትን ጥያቄዎች፣ የተካሔዱትን ክርክሮች፣ የታዩትን ዝንባሌዎችና የተወሰዱትን እርምጃዎች ይጠቁማል። እግረመንገዱን  ደራሲው የራሱን የእድገት ፣ የወዳጅነትና የታጋይነት ትዝታውን ያካፍለናል። ሆኖም ፣ የድርሰቱ ዋና ትኩረት ኀይሌ ፊዳ ላይ ነው። እንደሚታወቀው ኀይሌ ፊዳ በአውሮፓ የኢትዮጵያ ተማሪዎች ንቅናቄ ቀጥሎም የመኢሶን መሪ ነበር። የድርሰቱ ዓላማ የ ኀይሌ ፊዳን የአደባባይ አካልና አንደበት ለማመልከት ብቻ ሳይሆን መላ ሰውነቱን ለማሳየት ነው። ስለሆነም ስለ ኀይሌ ፊዳ ጨዋነት ፣ አስተዋይነትና ረቂቅነት ባሻገር ለዛውን እንዲሁም ልዩ ፍቅሩንና ስጦታውን በቋንቋ ፣ በስነጠበብና በሥነ ጽሁፍ ያስተዋውቀናል። የድህረ ዘውድ ኢትዮጵያን  የሁሉንም ዜጋ ነጻነትና እኩልነት የሚያረጋግጥ ፣ የደሀውንና የተበደለውን ወገን ዕድልና ጥቅም ቅድሚያ የሚሰጥ አቅጣጫ ከቀየሱት ዋና ወጣቶች ምሃል አንዱ ኀይሌ ፊዳ ነውና ይህን መልካም ማስታወሻ ስላብረከተልን ለአማረ ተግባሩ ባለውለታ ነን።

እንድሪያስ እሸቴ (ፕ/ር)

ሕይወቱ በአጭር የተቀጨው ወዳጄ ታሪክ ለሕዝብ ንባብ በመቅረቡ፣ በወቅቱ የነበርን ብቻ ሳንሆን ፣ ከእኛ በኋላ የመጡ ወደ ፊትም የሚመጡ ፣ በአብዮቱ አፍላ ዘመን ስለነበረው ሁኔታ ግንዛቤ እንዲጨብጡ ይና እንዲሁም በአብዮቱ ውስጥ ሚና ለነበረው ስለ ኀይሌ ፊዳ ኩማ መጠነኛ ግንዛቤ ያገኛሉ የሚል እምነት አለኝ። በአብዮቱ ወቅት ስለ ኀይሌ ፊዳ የነበረውን የዚያን ዘመን ወጣት ትውልድ እይታ በትክክለኛ መንገድ ለማንጸባረቅ ብሎም በወቅቱ የነበሩ ብዥታዎችን ለማጽዳት ፣ የተጣመመውን ለማስተካከል ይህች ትንሽ መጽሐፍ ከፍተኛ ተዋጽኦ ታደርጋለች የሚል ጽኑ እምነት አለኝ። ስለሆነውም ለደራሲው ከፍተኛ ምስጋና ይገባዋል።

ሽብሩ ተድላ ደስታ (ፕ/ር)

ይህችን ምጽሐፍ ለማንበብ ዕድሉን ማግኘቴ ወደኋላ ተመልሼ ኀይሌ ፊዳን እንዳስታውስ አድርጎኛል። ኀይሌ ፊዳ ማለት በርጋታና አርቆ አስተዋይነት አስደንጋጭና የከፋ ሁኔታዎችን ሳይቀር ለመተንተን ለማስረዳት ችሎታ ያለው ፣ ቋንቋው የበሰለና እውነትም የፖለቲካ መሪዎች ሊኖራቸው የሚገባ ብቃት ያለው ሰው ነበር።

አድማሱ ጣሰው (ዶ/ር)

 

BOOK DETAILS

Year : 2011

Price : 111.50

Type :  biography